Amharic Health Information

የሬስፒክሊክ አጠቃቀም (RespiClick)

በሬስፒክሊክ መልክ ተዘጋጅተው የሚመጡ መድሃኒቶች ዝርዝር

1. ፕሮኤር ሬስፒክሊክ (ProAir RespiClick)
2. ኤርዱዎ ሬስፒክሊክ (AirDuo RespiClick)
ፕሮኤር ሬስፒክሊክ (ProAir RespiClick)

ፕሮኤር (አልቢውትሮል) የተቆጡ እና የተዘጉ የአየር ቧንቧ ጡንቻዎችን በማፍታታት እና በመከፋፈት የአስም ህመምተኞች በቀላሉ ለመተንፈስ እንዲችሉ የሚረዳ መድሃኒት ነው። 

አልቢውተሮል በተለያየ ስም እና አስተሻሸግ ይመጣል። (ለምሳሌ ቬንቶሊን እና ፕሮቬንቲል) በኤች-ኤፍ-ኤ(HFA) ሜትር ዶዝ ኢንሄለር (MDI) ታሽገው ለሚመጡ የአልቢውትሮል አይነቶች ሌላ መማሪያ ይመልከቱ። ይህ መማሪያ የሚያገለግለው ለፕሮኤር ሬስፒክሊክ ነው።

ኤርዱዎ ሬስፒክሊክ (AirDuo RespiClick)

ኤርዱዎ ለአስም እና ሲኦፒዲ ታማማሚዎች በቀላሉ ለመተንፈስ እንዲረዳቸው የሚታዘዝ መድሃኒት ነው። የተዘጉ የአየር ቧንቧዎችን የሚከፍቱ ሁለት መድሃኒቶች፤ ማለትም ሳልሜትሮል እና ፍሉቲካሶል የተባሉ መድሃኒቶች ይይዛል።

ይህ መድሃኒት በተለያዩ መልኩ ይመረታል። አድቬር ኤርዱዎ፤ እንዲሁም አድቬር ኤች-ኤፍ-ኤ፤ እና አድቬር ዲስከስ ምሳሌ ናቸው። አስተሻሸጋቸው እና አጠቃቀማቸው የተለያየ ቢሆንም በውስጣቸው የሚይዙት አንድ አይነት መድሃኒት ነው። ይህ የአጠቃቀም መማሪያ የሚጠቅመው ለኤርዱዎ ሬስፒክሊክ ብቻ ነው።

ሬስፒክሊክ ኢንሄለሮችን ፕራይም ማደረግ (አስቀድሞ ማዘጋጀት) አያስፈልግም።

መድሃኒቱን ለመውሰድ

  1. የመድሀኒቱን እቃ ቀጥ አድርገው እንደያዙ ቢጫውን የመድሂኒት እቃ አፍ ክሊክየሚል ድምጽ እስኪሰሙ ድረስ ይክፈቱት። የመድሀኒቱን እቃ አፍ ደጋግሞ መክፈት መድሀኒቱን ያባክነዋል፤ የመድሀኒቱን እቃ ያበላሸዋል። ስለዚህ መድሀኒቱን ለመውሰድ ዝግጁ እስከሚሆኑ ድረስ የመድሀኒቱን እቃ አፍ አይክፈቱ። የመድሀኒቱን እቃ ሲከፍቱ (ከከፈቱ በሃላ) ቀጥ አድርገው መያዝ እንዳለቦት አይርሱ።
  2. የሚችሉትን ያህል ወደውጭ ይተንፍሱ።
  3. የመድሃኒቱን እቃ አፍ ወደከንፈርዎ ይውሰዱ። የመድሀኒቱን እቃ አፍ ዙርያ በከንፈርዎ ግጥም አድርገው ይያዙ። የመድሀኒቱን እቃ አናት ላይ ጣትዎ እንዳያርፍ እና ማስተንፈሻውን እንዳይሸፍን ይጠንቀቁ። ትክክለኛው አያያዝ ስእሉ ላይ እንደሚታየው የመድሃኒቱ እቃ ወገብ ላይ ነው።
  4. በፍጥነት እና በጥልቀት በአፍዎ ብቻ ወደሳንባዎ ይተንፍሱ
  5. የመድሀኒቱን እቃ አፍ ከከንፈርዎ ያንሱና ለአስር ሰከንድ ወይም የሚችሉትን ያህል ትንፋሽዎን ይያዙ።
  6. የመድሀኒቱን እቃ ክዳን ወደቦታው ይመልሱ።
  7. አፍዎን በውሃ ይጉመጥመጡ ውሃውን ይትፉ ይህን ማድረግ ትረሽ የተባለ በሽታ አፎዎት ውስጥ እንዳይፈጠር ይከላከላል።
የሬስፒክሊክ አጠቃቀም
የመድሃኒቱን እቃ ማጽዳት አያስፈልግም። ማጽዳት ካስፈለገ በደረቅ ሶፍት የመድሃኒቱን እቃ አፍ መወልወል ይቻላል። ሲያስቀምጡት ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።