Amharic Health Information

አትሮቬንት ኤች-ኤፍ-ኤ (Atrovent HFA)

የስኳር በሽታ - ዳያቤቲስ - Diabetes

አዲስ ካርቶን ሲከፍቱ

  • ካኒስተሩ በትክክል ከመሰኪያው ጋር በመደንብ መጣበቁን ያረጋግጡ።
  • ፕራይም ማድረግ አይርሱ።

ፕራይም ለማድረግ (ለማዘጋጀት)

አትሮቬንት መድሃኒት መጀምሪያ ከካርቶኑ ሲወጣ ፕራይም መደረግ (መዘጋጀት) አለበት። በተጨማሪ መድሃኒቱን ሳይወስዱ ሶስት ተከታታይ ቀን ካለፈ በተመሳሳይ መንገድ መድሃኒቱ ፕራይም መደረግ ያስፈልገዋል።  ፕራይም ማድረግ ትክክለኛውን የመድሃኒት መጠን እንዲወስዱ ይረዳዎታል።

ፕራይም የሚደረገው እንዲህ ነው፦

  1. የመድሃኒቱን ክዳን ይክፈቱ። የመድሃኒቱን አፍ ከፊትዎ ተቃራኒ አቅጣጫ ያዙሩት።
  2. የካኒስተሩን አናት በአመልካች ጣት፤ የመሰኪያውን ስር በአውራ ጣት፤ በማድረግ የመድሃኒቱን እቃ ይያዙት። አያያዙን ለመረዳት ከጎን ያለውን ምስል ይመልከቱ።
  3. የመድሃኒቱን አናት ሁለት ግዜ በመጫን መድሃኒቱ መውጣቱን ያረጋግጡ።

መድሃኒቱን ለመውሰድ

  1. መክደኛውን ይክፈቱና አለመቆሸሹን ወይም መድሃኒቱ እንዳይወጣ የሚያግደው ምንም ነገር እንደሌለ ያረጋግጡ።
  2. የሚችሉትን ያህል ወደውጭ ይተንፍሱ። ከአፍዎ ብቻ ሳይሆን ከሳንባዎ በደንብ አየር ለማስወጣት ይሞክሩ። መድሃኒቱን ከመውሰዶ በፊት መልሰው አየር ወደውስጥ አይተንፍሱ።
  3. የመድሃኒቱን እቃ ቀጥ አድርገው ይያዙና የመድሃኒቱን እቃ አፍ ዙርያ በከንፈርዎ ገጥመው ይያዙ።
  4. በእርጋታ እና በጥልቀት ወደሳንባዎ እየተነፈሱ የመድሃኒቱን እቃ አናት ይጫኑ።
  5. መድሃኒቱ አንዴ እንደተረጨ የመድሃኒቱን አናት ይልቀቁ።
  6. መድሃኒቱን ወደሳንባዎ ከሳቡ በሃላ የመድሃኒቱን አፍ ከአፍዎ ያውጡና ለአስር ሰከንድ ወይም እስከሚችሉት ድረስ ትንፋሽዎን ይያዙ።
  7. ሁለት ግዜ መድሃኒቱን እንዲወስዱ ከታዘዙ፤ ቢያንስ አስራ አምስት ሰከንድ ይጠብቁና ከ1 – 6 ያደረጉትን ይድገሙ።
  8. መድሃኒቱን ወስደው ሲጨርሱ፤ ክዳኑን በቦታው መመለስዎን አይርሱ።

የመድሃኒቱን እቃ እንዴት እንደሚያጸዱ

ካኒስተሩን ያውጡ። የካንሰተሩን መሰኪያ ላይ ለብ ያለ ውሃ ለሰላሳ ሰከንድ ያፍስሱበት። እንዲደርቅ ንጹህ ቦታ ያስቀምጡት። በጨርቅ ወይም በሶፍት ለማድረቅ አይሞክሩ። በየሳምንቱ ማጽዳት ይቻላል።

ማጣቀሻ

ATROVENT HFA[package insert]. Princeton, Ridgefield, CT 06877 USA: Boehringer Ingelheim Pharmaceuticals, Inc.; 2020.

1 thought on “አትሮቬንት ኤች-ኤፍ-ኤ (Atrovent HFA)”

Comments are closed.