Amharic Health Information

አድቬር ዲስከስ (Advair Diskus)

የመድሃኒት ስም ጀነሪክ፦ ሜትፎርሚን (Metformin)

ምድብ፦ ባይጉዋናይድ

ብራንድ ስም ግሉኮፌጅ (Glucophage)፣ ፎርታሜት (Fortamet) ወይም ግሉሜትዛ (Glumetza) እና ሌሎች

አድቬር ምንድነው?

አድቬር ለአስም እና ሲኦፒዲ ታማማሚዎች በቀላሉ ለመተንፈስ እንዲረዳቸው የሚታዘዝ መድሃኒት ነው።  የተዘጉ የአየር ቧንቧዎችን የሚከፍቱ ሁለት መድሃኒቶች፤ ማለትም ሳልሜትሮል እና ፍሉቲካሶል የተባሉ መድሃኒቶች ይይዛል። አድቬር በተለያዩ መልኩ ይመረታል። አድቬር ኤርዱዎ፤ አድቬር ሪስፒክሊክ፤ እንዲሁም አድቬር ኤች-ኤፍ-ኤ፤ እና አድቬር ዲስከስ የአድቬር አይነቶች ምሳሌ ናቸው።  አስተሻሸጋቸው እና አጠቃቀማቸው የተለያየ ቢሆንም በውስጣቸው የሚይዙት አንድ አይነት መድሃኒት ነው። ይህ የአጠቃቀም መማሪያ የሚጠቅመው ለአድቬር ዲስከስ ብቻ ነው።

አድቬር ዲስከስ

መድሃኒቱን ለመውሰድ

  1. ምስሉ ላይ እንደሚታየው በግራ መደፍዎ የመድሃኒቱን እቃ አጋድመው ይያዙት። የመድሃኒቱን እቃ እፍ ለመክፈት መሸፈኛውን በቀኝ እጅዎ ከራስዎ ተቃራኒ እቅጣጫ እስከመጨረሻው ድረስ ይግፉት። ይህን ግዜ የመድሃኒቱ አፍ ይታያል።

2. የመድሃኒቱን አፍ ወደራስዎ ያዙሩት። ከመድሃኒቱ እቃ አፍ አጠገብ የምትገኘውን መክፈቻ ከራስዎ በተቃራኒ አቅጣጫ ክሊክ የሚል ድምጽ እስከሚሰሙ ድረስ ያዙሩት። በዚህ ግዜ የመድሃኒቱ ዱቄት ቦታው ይገባል። ከዚህ በሃላ የመድሃኒትን እቃ እንደተጋደመ ይያዙት። በሃይል ማንቀሳቀስ ቦታው የገባውን ዱቄት መድሃኒት እንዲፈስ ያደርገዋል።

3. መድሃኒቱን ከመሳቦ በፊት የሚችሉትን ያህል ወደውጭ ይተንፍሱ። ወደመድሃኒቱ እቃ አፍ እንዳይተነፍሱ ይጠነቀቁ።

4. የመድሃኒቱን እቃ አፍ በከንፈርዎ ገጥመው ይያዙና በፍጥነት እና በጥልቀት ወደሳምባዎ ይተንፍሱ። በአፍንጫዎ አይተንፍሱ።

5. የመድሃኒቱን እቃ አፍ ከአፍዎ ያውጡና ለአስር ሰከንድ ወይም የሚችሉትን ያህል ትንፋሽዎን ይዘው ይቆዩ። ከዚህ በሃላ በእርጋታ ወደውጭ ይተንፍሱ።

6. የዲስከሱን ክዳን ወደቦታው ይመልሱ። በትክክል መከደኑን የሚያውቁት ክሊክ የሚል ድምጽ ሲሰሙ ነው።

7. አፍዎን በውሃ ይጉመጥመጡና ውሃውን ይትፉት። ይህን ማድረግ ትረሽ የተባለ በሽታ አፎዎት ውስጥ እንዳይፈጠር ይከላከላል።

8. የመድሃኒቱን እቃ ማጽዳት አያስፈልግም። ሲያስቀምጡት ደረቅ ቦታ አጋድመው ያስቀምጡት።

መድሃኒቴን መዋጥ ከረሳሁ ምን ማድረግ አለብኝ?

ወድያው እንዳስታወሱ ይውሰዱ። ብዙ ሰአት ካለፈ ግን ይተውት እና በሚቀጥለው የመድሃኒት መውሰጃ ግዜዎ የተለመደውን መጠን ይውሰዱ። የረሱትን ጨምረው መውሰድ የለብዎትም።

በዚህ መድሃኒት ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች

ሜትፎርሚን የሚወስዱ ሰዎች ብዙ ግዜ ይስማማቸዋል። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ሜትፎርሚን ሲወስዱ የሆድ ህመም ሊያጋጥማቸው ይችላል። ለምሳሌ ያህል ተቅማጥ/ድርቀት፣ የምግብ አለመንሸራሸር፣ ፈስ እና ሆድ መጮህ፣ አፍ ላይ የብረት ጣእም እንዲሁም ሆድን የመጭነቅ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል።ይህ ምልክት ከግዜ በሃላ ይጠፋል። ከምግብ ጋር መውሰድ እነዚህን ምልክቶችን ለመቀነስ ይረዳል። ከሚችሉት በላይ ከሆነ ሃኪምዎን ያማክሩ።

አንዳንድ ዘግይቶ የሚሰራ (ግሉኮፌጅ ኤክስ-አር (Glucophage XR)፣ ፎርታሜት (Fortamet) ወይም ግሉሜትዛ (Glumetza)) የተባሉት የሜትፎርሚን መድሀኒቶች የሚወስዱ ሰዎች በሰገራ ውስጥ ክኒን የሚመስል ነገር ሊያዩ ይችላሉ። ይህ ምንም ችግር የለውም።

ማጣቀሻ

ADVAIR DISKUS [package insert]. GlaxoSmithKline, Research Triangle Park, NC 27709; 2019.

ቀን: 06/29/20