የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ለሰውነት እድገት፣ ግንባታና ጉልበት አስፈላጊ ነው። አንዲት ሴት በእርግዝና ግዜ የተሟሏ ምግብ ካልተመገበች ክብደቱ ከተለመደው በታች የሆነ ህጻን ከመውለድ ባሻገር የእናትየዋን የአጥንት እና የደም ጤንነት ሊያውክ ይችላል። ይህ እንዳይሆን ፎሊክ አሲድ(folic acid)፣ ቫይታሚን ዲ(vitamin D) እና ካልስየም(calcium)፣ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በክኒን መልክ መውሰድ ይመከራል። ይህም አንዲት እርጉዝ ሴት በቀን ማግኘት ያለባት ቫይታሚንና ሚነራል መጠን የተሟላ ያደርገዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ »