Amharic Health Information

አልቢውትሮል (Albuterol sulfate HFA)

አልቢውትሮል ምንድነው?

አልቢውትሮል የተቆጡ እና የተዘጉ የአየር ቧንቧ ጡንቻዎችን በማፍታታት እና በመከፋፈት የአስም ህመምተኞች በቀላሉ ለመተንፈስ እንዲችሉ የሚረዳ መድሃኒት ነው። አልቢውተሮል በተለያየ ስም እና አስተሻሸግ ይመጣል።

አልቢውትሮል፤ ቬንቶሊን ች-ኤፍ-ኤ (Ventolin HFA)፣ ፕሮኤር ች-ኤፍ-ኤ (ProAir HFA)፣ ፕሮቬንቲል ኤች-ኤፍ-ኤ (Proventil HFA) በሚባሉ ስሞች ይመረታል። እነዚህ ከአልቢውትሮል ጋር አጠቃቀማቸው እና አስተሻሸጋቸው ተመሳሳይ ነው። አልቢውተሮል በሶሉውሽን፣ በዲጂሄለር፣ ሬስፒክሊክ እና ሌሎች ውስጣቸው የሚይዘው አልቢውትሮል ቢሆንም አጠቃቀማቸው ለየት ይላል።

ይህ መማሪያ የሚያገለግለው በኤች-ኤፍ-ኤ (HFA) ሜትር-ዶዝ-ኢንሄለር(MDI) መልኩ ታሽጎ ሊመጣ የአልቢውተሮል ብራንድ እና ጀነሪክ መድሃኒቶች ነው። ይህንን ለማወቅ ከመድሃኒቱ ስም አጠገብ ኤች-ኤፍ- ኤ(HFA) የሚል ጽሁፍ እንዳለ አረጋግጡ።

አዲስ ካርቶን ሲከፍቱ  ፕራይም ማድረግ አይርሱ።

ፕራይም ማድረግ መድሃኒቱን ሲወስዱ ትክክለኛውን መጠን እንዲወስዱ ይረዳዎታል።

ፕራይም ለማድረግ

  1. ካኒስተሩ በትክክል ከመሰኪያው ጋር በመደንብ መጣበቁን ያረጋግጡ።
  2. የመድሃኒቱን እቃ በሚገባ ይበጥብጡ።
  3. የመድሃኒቱን ክዳን ይክፈቱና ከፊትዎ ተቃራኒ አቅጣጫ ያዙሩት።
  4. የካኒስተሩን አናት በአመልካች ጣት፤ የመሰኪያውን ስር በአውራ ጣት፤ በማድረግ የመድሃኒቱን እቃ ይያዙ አያያዙን ለመረዳት ከስር ያለውን ምስል ይመልከቱ።
  1. የመድሃኒቱን አናት በመጫን መድሃኒቱ መረጨቱን ያረጋግጡ።

ለቬንቶሊን

4 ግዜ መድሃኒቱን ይርጩ

መድሃኒቱን ከካርቶኑ ሲያወጡ፣ መድሃኒቱን ሳይወስዱ አስራ አራት ቀን ካለፈ፣ የመድሃኒቱ እቃ ከወደቀ ድጋሚ ፕራይም ማድረግ ያስፈልጋል።

ለፕሮኤር

3 ግዜ መድሃኒቱን ይርጩ

መድሃኒቱን ከካርቶኑ ሲያወጡ፣ መድሃኒቱን ሳይጠቀሙ ሁለት ሳምንት ካለፈ ድጋሚ ፕራይም ማድረግ ያስፈልጋል።

ለፕሮቬንቲል

4 ግዜ መድሃኒቱን ይርጩ

መድሃኒቱን ከካርቶኑ ሲያወጡ ፣ መድሃኒቱን ሳይጠቀሙ ለሁለት ሳምንት ከቆዩ ድጋሚ ፕራይም ማድረግ ያስፈልጋል።

  1. በዚህ ግዜ የመድሃኒቱ እቃ መቁጠሪያ ፕራይም ባደረጉበት ቁጥር እኩል መቀነሱን ያስተውሉ። (የፕሮኤር መቁጠሪያ መድሃኒቱን ሶስት ግዜ ፕራይም እስኪያረጉት ድረስ በቁጥር ፈንታ ዶት(.) ብቻ ያሳያል።)

መድሃኒቱን ለመውሰድ

  1. መድሃኒቱን ከመውሰዶ በፊት ለአምስት ሰከንድ ያህል መድሃኒቱን በሚገባ በጥብጡ።
  2. መክደኛውን ይክፈቱና አለመቆሸሹን ወይም መድሃኒቱ እንዳይወጣ የሚያግደው ምንም ነገር እንደሌለ ያረጋግጡ።
  3. የሚችሉትን ያህል ወደውጭ ይተንፍሱ። ከአፍዎ ብቻ ሳይሆን ከሳንባዎ በደንብ አየር ለማስወጣት ይሞክሩ። መድሃኒቱን ከመውሰዶ በፊት መልሰው አየር ወደውስጥ አይተንፍሱ።
  4. የመድሃኒቱን እቃ ቀጥ አድርገው ይያዙና የመድሃኒቱን እቃ አፍ ዙርያ በከንፈርዎ ግጥም አድርገው ይያዙ።
  5. በእርጋታ እና በጥልቀት ወደሳንባዎ እየተነፈሱ የመድሃኒቱን እቃ አናት ይጫኑ። መድሃኒቱ አንዴ እንደተረጨ የመድሃኒቱን አናት ይልቀቁ። መድሃኒቱን ወደሳንባዎ ከሳቡ በሃላ የመድሃኒቱን አፍ ከአፍዎ ያውጡና ለአስር ሰከንድ ወይም እስከሚችሉት ድረስ ትንፋሽዎን ይያዙ።
  6. ሁለት ግዜ መድሃኒቱን እንዲስቡ ከታዘዙ፤ አንድ ደቂቃ ይጠብቁና ከ3 – 5 ያደረጉትን ይድገሙ።
  7. መድሃኒቱን ወስደው ሲጨርሱ፤ ክዳኑን በቦታው መመለስዎን አይርሱ።

የመድሃኒቱን እቃ እንዴት እንደሚያጸዱ

ቬንቶሊን እና ፕሮቬንቲል፦ ካኒስተሩን ከማቀፊያው ያውጡ። በካንሰተሩ ማቀፊያ ለብ ያለ ውሃ ለሰላሳ ሰከንድ ያፍስሱበት። በራሱ እንዲደርቅ ንጹህ ቦታ ያስቀምጡት። በጨርቅ ወይም በሶፍት ለማድረቅ አይሞክሩ። በየሳምንቱ ማጽዳት ይቻላል።

ለፕሮኤር፦  ካኒስተሩን ከማቀፊያው ያውጡ። ማቀፊያውን እና አፉን በውሃ ያጽዱት። በአየር እንዲደርቅ ንጹህ ቦታ ይስቀምጡት። ካኒስተሩን ወደማቀፊያው ሲመልሱ በሚገባ መግጠሙን ያረጋግጡ። እንደአስፈላጊነቱ በየሳምንቱ ማጽዳት ይቻላል።

ለሁሉም፦ ካኒስተሩ ውሃ ወይም እርጥበት እንዳያገኘው ይጠንቀቁ።

ማጣቀሻ

PROAIR HFA[package insert]. Waterford, Ireland:IVAX Pharmaceuticals; 2016.