የስትሮክ ምልክቶችን ያውቃሉ?
“FAST”
የሚለውን ቃል ያስታውሱ!!F
Face
ፊት
የፊት አንድ ጎን መደንዘዝ
ፈገግ ለማለት ሲሞክሩ ፈገግ ማለት አለመቻል ወይም አንድ የከንፈር ጫፍ ወደላይ ሌላኛው ወደታች መቀልበስ
A
Arms
እጅ
የአንድ እጅ መዛል
ሁለቱንም እጅ ከፍ ለማድረስ ሲሞክሩ አንድ እጅ አልታዘዝ ማለት። ሁለቱንም እጅ ከፍ ማድረግ ይችላሉ፤ ነገር ግን አንድ እጅ ዝሎ ወደታች ይወርዳል።
S
Speech
አነጋገር
የአነጋገር መጎተት
መናገር ይከብዳል የሚናገሩት ነገር ትርጉም አይሰጥም ቀላል አርፍተ ነገር ደግመው እንዲናገሩ ሲጠየቁ ለመድገም ይቸገራሉ።
T
Time to hospital
ሰአት
በተቻለ ፍጥነት ሆስፒታል መሄድ
እነዚህ ለውጦች በድንገት ሲታዩ ቶሎ ወደሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል።
ከነዚህ ውጭ ሌሎች የስትሮክ ምልክቶች
♦ ድንገት የሰውነት መደንዘዝ ወይም በግማሽ የሰውነት ክፍል ሰውነትን ማዘዝ አለመቻል።
♦ ድንገተኛ የማገናዘብ ችሎታ መቀነስ፣ ለመናገር መቸገር ወይም ሌላ ሰው የሚናገረውን መረዳት አለመቻል
♦ ድንገት የማየት ችሎታን ማጣት
♦ ድንገት መራመድ አለመቻል ወይም የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል
♦ ድንገተኛ፣ ምንም ምክንያት የሌለው ሀይለኛ ራስምታት ናቸው።
ህክምና ለማግኘት የሚፈጀው እያንዳንዱ ደቂቃ ለውጥ ያመጣል በአንጎል ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እና ህክምና ለማግኘት ምልክት ከታየ በሶስት ሰአት ውስጥ ሆስፒታል መድረስ ያስፈልጋል።
ማጣቀሻ
Adapted from American Heart Association at https://www.stroke.org/en/about-stroke/stroke-symptoms (Aug 4, 2019)
ቀን: Aug 9, 2020
በቅርብ ግዜ የወጡ ጽሁፎች
- ስኳር በሽታ
የስኳር በሽታ በደም ውስጥ ከመጠን በላይ ግሉኮስ ሲኖር የሚፈጠር በሽታ ነው። የዚህ መንስኤ በተፈጥሮ ከጣፊያ…
- በእርግዝና ግዜ የሚያስፈልጉ ቫይታሚኖች እና ሚነራሎች
የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ለሰውነት እድገት፣ ግንባታና ጉልበት አስፈላጊ ነው። አንዲት ሴት በእርግዝና ግዜ የተሟሏ ምግብ…
- አስም
አስም የመተንፈሻ ትቦ ህመም ነው። የአስም ህመም የሚከሰተው የመተንፈሻ ቱቦ ሲቆጣ እና ሲጠብ ነው። ይህ…
5 thoughts on “የስትሮክ ምልክቶችን ያውቃሉ?”
Comments are closed.