ቫይታሚን ኤ (Vitamin A) September 21, 2020September 21, 2020 by Admin ፕሪንት ለማድረግ ይህን ይጫኑ ቫይታሚን ኤ (Vitamin A)ለአይን ጤንነትየተሟላ የበሽታ መቋቋም ችሎታየሳንባ እና የኩላሊት ጤንነት ላይ ሚና አለው። ቫይታሚን ኤ ብዙ ምግቦች ውስጥ ይገኛል የሚገኘውም በሁለት የተለያዩ አይነቶች ነው።ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ (Preformed vitamin A) በከብቶች ስጋ በዶሮ ስጋ በወተት እንዲሁም በወተት ተረፈ ምግቦች ውስጥ ይገኛል።ፕሮቫይታሚን ኤ (Provitamin A) በፍራፍሬዎች እና አታክልቶች ውስጥ ይገኛል። ቤታ ካሮቲን (Beta carotine) በተፈጥሮ በብዛት የሚገኝ የፕሮቫይታሚን አይነት ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ኤ የሚይዙ ምግቦች የበሬ ጉበትእንደሳልመን ያሉ የአሳ አይነቶችአረንጋዴ ቅጠል ያላቸው አታክልቶችአረንጋዴ፣ ብርቱካናማ እንዲሁም ቢጫ ቀለም ያላቸው አታክልቶች ለምሳሌ ካሮት እና ብሮክሊማንጎ እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ናቸው።የተሟላ ዝርዝር በዚህ ድረገጽ ያገኛሉ https://ods.od.nih.gov/pubs/usdandb/VitA-betaCarotene-Content.pdf በቀን ለሰው የሚያስፈልገው የቫይታሚን መጠን እንደ እድሜ ክልል እና ጾታ የተለያየ ነው። የቫይታሚን ኤ መጠን በማይክሮ ግራም ሬቲኖል አክቲቪቲ ኢኩቫለንት (mcg of RAE) ይለካል።የሚከተለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ ቫይታሚን ኤ (Vitamin A) በመድሃኒት መልክ ይሸጣል? በክኒን መልኩ የሚሸጡ ቫይታሚን ኤ ውጤቶች በብዛት ይገኛሉ። በተጨማሪ ቤታ ካሮቲን (Beta carotine)፣ ሬቲናይል አሲቴት (Retinyl acetate)፣ ወይም ፕሮቫይታሚን ኤ (Provitamin A) በሚል ስም ሊሸጡ ይችላሉ። ብዙ መልቲቫይታሚኖች በውስጣቸው ቫይታሚን ኤ ያካትታሉ። ቫይታሚን ኤ ሲያንስ ምን ምልክት ይታያል? የቫይታሚን ኤ እጥረት ዋንኛ ምልክት የአይን ህመም ነው። ይህ የአይን ህመም ዳፍንት ወይም ዚራፍታልሚያ (Xerophthalmia) ይባላል። ዚራፍታልሚያ ያለባቸው ሰዎች በቂ ብርሃን በሌለበት ቦታ የማየት ችሎታቸው ይቀንሳል። ህጻናቶች፣ እርጉዝ እና የሚያጠቡ ሴቶች ለዚህ የተጋለጡ ናቸው። ሲስቲክ ፋይብሮሲስ (Cystic fibrosis) የሚባል ህመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁ የዚህ ቫይታሚን እጥረት ሊያጋጥማቸው ይችላል። ይህ ቫይታሚን ሲበዛ ይጎዳል? በተፈጥሮ መልክ ከምግብ የሚገኝ ቫይታሚን ሰውነት ላይ ጉዳት አያደርስም። ነገር ግን ከሚመከረው መጠን በላይ በክኒን መልኩ ሲወሰዱ አንዳንድ የቫይታሚን ኤ አይነቶች ለሰውነት ጉዳት ሊኖራቸው ይችላል።ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ ከልክ በላይ ሲወሰድ የማዞር፣ የማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም የራስ ምታት ስሜት እንዲሰማ ሊያደርግ ይችላል። ከዛም በላይ ኮማ ሊያስገባ ሲብስም ለሞት ሊዳርግ ይችላል። እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ከልክ በላይ ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ ሲወስዱ በጽንሱ ላይ የአካል ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በዚህ ምክንያት ያለሀኪም ትእዛዝ እርጉዝ የሆኑ ሰዎች ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ እንዲወስዱ አይመከርም።ሌሎች የቫይታሚን ኤ አይነቶች ማለትም ፕሮቫይታሚን ኤ እና ቤታ ካሮቲን በሰውነት ውስጥ ከሚገባው በላይ ሲገኝ የቆዳን ቀለም ወደ ቢጫ ወይም ብርቱካናማ ቀለም ሊለውጥ ይችላል። እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ይህንን አይነት የቫይታሚን ኤ አይነት ሲወስዱ በጽንስም ሆነ በእናት ጤና ላይ ጉዳት አያደርስም። ማጣቀሻ Office of Dietary Supplements – Vitamin A. (2020, February 14). Retrieved September 10, 2020, from https://ods.od.nih.gov/factsheets/VitaminA-Consumer/ ቀን: Sep, 21, 2020 በቅርብ ግዜ የወጡ ጽሁፎች አትሮቬንት ኤች-ኤፍ-ኤ (Atrovent HFA)መድሃኒቱን ለመውሰድ መክደኛውን ይክፈቱና አለመቆሸሹን ወይም መድሃኒቱ እንዳይወጣ የሚያግደው ምንም ነገር እንደሌለ ያረጋግጡ። የሚችሉትን ያህል… በእርግዝና ግዜ የሚያስፈልጉ ቫይታሚኖች እና ሚነራሎችየተመጣጠነ ምግብ መመገብ ለሰውነት እድገት፣ ግንባታና ጉልበት አስፈላጊ ነው። አንዲት ሴት በእርግዝና ግዜ የተሟሏ ምግብ… ስኳር በሽታየስኳር በሽታ በደም ውስጥ ከመጠን በላይ ግሉኮስ ሲኖር የሚፈጠር በሽታ ነው። የዚህ መንስኤ በተፈጥሮ ከጣፊያ…