Amharic Health Information

የስትሮክ ምልክቶችን ያውቃሉ?​

የስትሮክ ምልክቶችን ያውቃሉ?

የስትሮክ ምልክቶችን ለመለየት

“FAST”

የሚለውን ቃል ያስታውሱ!!

F

Face

ፊት

የፊት አንድ ጎን መደንዘዝ

ፈገግ ለማለት ሲሞክሩ ፈገግ ማለት አለመቻል ወይም አንድ የከንፈር ጫፍ ወደላይ ሌላኛው ወደታች መቀልበስ

A

Arms

እጅ

የአንድ እጅ መዛል

ሁለቱንም እጅ ከፍ ለማድረስ ሲሞክሩ አንድ እጅ አልታዘዝ ማለት። ሁለቱንም እጅ ከፍ ማድረግ ይችላሉ፤ ነገር ግን አንድ እጅ ዝሎ ወደታች ይወርዳል።

S

Speech

አነጋገር

የአነጋገር መጎተት

መናገር ይከብዳል የሚናገሩት ነገር ትርጉም አይሰጥም ቀላል አርፍተ ነገር ደግመው እንዲናገሩ ሲጠየቁ ለመድገም ይቸገራሉ።

T

Time to hospital

ሰአት

በተቻለ ፍጥነት ሆስፒታል መሄድ

እነዚህ ለውጦች በድንገት ሲታዩ ቶሎ ወደሆስፒታል መሄድ ያስፈልጋል።

ከነዚህ ውጭ ሌሎች የስትሮክ ምልክቶች ​

♦ ድንገት የሰውነት መደንዘዝ ወይም በግማሽ የሰውነት ክፍል ሰውነትን ማዘዝ አለመቻል።

♦ ድንገተኛ የማገናዘብ ችሎታ መቀነስ፣ ለመናገር መቸገር ወይም ሌላ ሰው የሚናገረውን መረዳት አለመቻል

♦ ድንገት የማየት ችሎታን ማጣት

♦ ድንገት መራመድ አለመቻል ወይም የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል

♦ ድንገተኛ፣ ምንም ምክንያት የሌለው ሀይለኛ ራስምታት ናቸው።

 

ህክምና ለማግኘት የሚፈጀው እያንዳንዱ ደቂቃ ለውጥ ያመጣል በአንጎል ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እና ህክምና ለማግኘት ምልክት ከታየ በሶስት ሰአት ውስጥ ሆስፒታል መድረስ ያስፈልጋል።

ማጣቀሻ 

Adapted from American Heart Association at https://www.stroke.org/en/about-stroke/stroke-symptoms (Aug 4, 2019)

 

 

ቀን: Aug 9, 2020