Amharic Health Information

ቫይታሚን ኤ (Vitamin A)

ቫይታሚን ኤ ​ (Vitamin A)

  • ለአይን ጤንነት
  • የተሟላ የበሽታ መቋቋም ችሎታ
  • የሳንባ እና የኩላሊት ጤንነት ላይ ሚና አለው።

ቫይታሚን ኤ ብዙ ምግቦች ውስጥ ይገኛል

የሚገኘውም በሁለት የተለያዩ አይነቶች ነው።

  1. ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ (Preformed vitamin A) በከብቶች ስጋ በዶሮ ስጋ  በወተት እንዲሁም በወተት ተረፈ ምግቦች ውስጥ ይገኛል።
  2. ፕሮቫይታሚን ኤ (Provitamin A) በፍራፍሬዎች እና አታክልቶች ውስጥ ይገኛል። ቤታ ካሮቲን (Beta carotine) በተፈጥሮ በብዛት የሚገኝ የፕሮቫይታሚን አይነት ነው።

ከፍተኛ መጠን ያለው ቫይታሚን ኤ የሚይዙ ምግቦች

  • የበሬ ጉበት
  • እንደሳልመን ያሉ የአሳ አይነቶች
  • አረንጋዴ ቅጠል ያላቸው አታክልቶች
  • አረንጋዴ፣ ብርቱካናማ እንዲሁም ቢጫ ቀለም ያላቸው አታክልቶች ለምሳሌ ካሮት እና ብሮክሊ
  • ማንጎ እና ሌሎች ፍራፍሬዎች ናቸው።

የተሟላ ዝርዝር በዚህ ድረገጽ ያገኛሉ https://ods.od.nih.gov/pubs/usdandb/VitA-betaCarotene-Content.pdf

በቀን ለሰው የሚያስፈልገው የቫይታሚን  መጠን እንደ እድሜ ክልል እና ጾታ የተለያየ ነው። የቫይታሚን ኤ መጠን በማይክሮ ግራም ሬቲኖል አክቲቪቲ ኢኩቫለንት (mcg of RAE) ይለካል።
የሚከተለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ

ቫይታሚን ኤ (Vitamin A) በመድሃኒት መልክ ይሸጣል?

በክኒን መልኩ የሚሸጡ ቫይታሚን ኤ ውጤቶች በብዛት ይገኛሉ። በተጨማሪ ቤታ ካሮቲን (Beta carotine)፣ ሬቲናይል አሲቴት (Retinyl acetate)፣ ወይም ፕሮቫይታሚን ኤ (Provitamin A) በሚል ስም ሊሸጡ ይችላሉ። ብዙ መልቲቫይታሚኖች በውስጣቸው ቫይታሚን ኤ ያካትታሉ።

ቫይታሚን ኤ ሲያንስ ምን ምልክት ይታያል?

የቫይታሚን ኤ  እጥረት ዋኛ ምልክት የአይን ህመም ነው። ይህ የአይን ህመም ዳፍንት ወይም ዚራፍታልሚያ (Xerophthalmia) ይባላል። ዚራፍታልሚያ ያለባቸው ሰዎች በቂ ብርሃን በሌለበት ቦታ የማየት ችሎታቸው ይቀንሳል። ህጻናቶች፣ እርጉዝ እና የሚያጠቡ ሴቶች ለዚህ  የተጋለጡ ናቸው። ሲስቲክ ፋይብሮሲስ (Cystic fibrosis) የሚባል ህመም ያለባቸው ሰዎች እንዲሁ የዚህ  ቫይታሚን  እጥረት ሊያጋጥማቸው ይችላል።

ይህ ቫይታሚን ሲበዛ ይጎዳል?

በተፈጥሮ መልክ ከምግብ የሚገኝ ቫይታሚን  ሰውነት ላይ ጉዳት አያደርስም። ነገር ግን  ከሚመከረው መጠን በላይ በክኒን መልኩ ሲወሰዱ አንዳንድ የቫይታሚን ኤ አይነቶች ለሰውነት ጉዳት ሊኖራቸው ይችላል።

ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ ከልክ በላይ ሲወሰድ የማዞር፣ የማቅለሽለሽ፣ እንዲሁም የራስ ምታት ስሜት እንዲሰማ ሊያደርግ ይችላል። ከዛም በላይ ኮማ ሊያስገባ ሲብስም ለሞት ሊዳርግ ይችላል። እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ከልክ በላይ ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ ሲወስዱ በጽንሱ ላይ የአካል ጉዳት ሊያደርስ ይችላል። በዚህ ምክንያት ያለሀኪም ትእዛዝ እርጉዝ የሆኑ ሰዎች ፕሪፎርምድ ቫይታሚን ኤ እንዲወስዱ አይመከርም

ሌሎች የቫይታሚን ኤ አይነቶች ማለትም ፕሮቫይታሚን ኤ እና ቤታ ካሮቲን በሰውነት ውስጥ ከሚገባው በላይ ሲገኝ የቆዳን ቀለም ወደ ቢጫ ወይም ብርቱካናማ ቀለም ሊለውጥ ይችላል። እርጉዝ የሆኑ ሴቶች ይህንን አይነት የቫይታሚን ኤ አይነት ሲወስዱ በጽንስም ሆነ በእናት ጤና ላይ ጉዳት አያደርስም።

 

ቀን:  Sep, 21, 2020