Amharic Health Information

እርግዝና እና ልጆች

ህጻናት

  • ትኩሳት በህጻናት ላይ
    ትኩሳት ሰውነት ከጎጂ ባክቴርያዎች እና ሌሎች ተውሳኮች ራሱን በሚከላከልበት ጊዜ የሚፈጠር የሰውነት ሙቀት መጨመር ነው። ጤነኛ የሆነ ህጻን የሰውነት ሙቀት 97 እስከ 100.4 ዲግሪ ፋራናይት(36.1 እስከ 38 ዲግሪ ሴልሸስ) ነው።ተጨማሪ ያንብቡ »

የእናቶች ጤና

  • ድሮስፓይርኖን/ኤትናይል ኤስትርዳዮል
    ድሮስፓይርኖን/ኤትናይል ኤስትርዳዮል (Drospirenone/ethinyl estradiol) እንቁላል ወደ ማህፀን እንዳይወጣ በማድረግ (by preventing ovulation) እርግዝናን ይከላከላል። በተጨማሪ ጽንስ እንዳይፈጠር የማህጸን ግድግዳ እና የማህጸን ፈሳሽ ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። ይህ ክኒን ሁለት መድሀኒቶችን በውስጡ ይይዛል። የመጀመሪያው ድሮስፓይርኖን (Dospirenone) ሲሆን ሁለተኛው ኢትናይል ኤስትርዳዮል (Ethinyl estradiol) ነው።ተጨማሪ ያንብቡ »
  • በእርግዝና ግዜ የሚያስፈልጉ ቫይታሚኖች እና ሚነራሎች
    የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ለሰውነት እድገት፣ ግንባታና ጉልበት አስፈላጊ ነው። አንዲት ሴት በእርግዝና ግዜ የተሟሏ ምግብ ካልተመገበች ክብደቱ ከተለመደው በታች የሆነ ህጻን ከመውለድ ባሻገር የእናትየዋን የአጥንት እና የደም ጤንነት ሊያውክ ይችላል። ይህ እንዳይሆን ፎሊክ አሲድ(folic acid)፣ ቫይታሚን ዲ(vitamin D) እና ካልስየም(calcium)፣ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን በክኒን መልክ መውሰድ ይመከራል። ይህም አንዲት እርጉዝ ሴት በቀን ማግኘት ያለባት ቫይታሚንና ሚነራል መጠን የተሟላ ያደርገዋል።ተጨማሪ ያንብቡ »

ከቤተሰብ ጤና ጋር የተያያዙ መድሃኒቶች፣ ምግቦች፣ እና ሌሎች ጥንቃቄዎች