Amharic Health Information

የሞደርና ኮቪድ 19 ክትባት

ኮቪድ 19 በሳርስ ኮቪድ 2 ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው። በዋነኝነት መተንፈሻ አካላትን ያጠቃል። ነገር ግን ሌሎች የሰውነት ክፍሎችንም ሊያጠቃ ይችላል። በሽታው ከታየበት የ2019 አመት ጀምሮ ያደረሰውን ሞት የማህበረሰባዊ እና የኢኮኖሚ ችግር ለማረጋጋት በተደረገው የምርምር ጥረት ፍሬ ካሳዩት እና ልዩ ፍቃድ ያገኙ ሁለት ክትባቶች መካከል የሞደርና ኮቪድ 19 ክትባት አንዱ ነው።

የሞደርና ኮቪድ-19 ክትባት ከ 18 አመት እድሜ በላይ ለሆኑ ሰዎች  በጡንቻ በኩል በመርፌ የሚሰጥ ክትባት ነው። ክትባቱን ለሟሟላት አንድ ሰው ሁለት ጊዜ መከተብ አለበት። ሁለተኛው ክትባት የሚሰጠው የመጀመሪያው ከተወሰደ (ቢያንስ) አንድ ወር በሁዋላ ነው።

የክትባቱ ጥቅም

እስካሁን በተደረገው ጥናት መሰረት ይህ ክትባት የኮቪድ-19 በሽታን ለመከላከል ይረዳል ተብሎ ይታሰባል።

የሞደርና ኮቪድ 19 ክትባት እንዴት ነው የሚሰራው?

የክትባቱ ዋነኛ አካል ሞድ-አርኤንኤ (ModRNA) ነው። ይህ ሜሴንጀር አርኤንኤ(mRNA) በሰው ተህዋስ (Cell) ውስጥ የኮቪድ 19 ቫይረስን የሚመስል ስፓይክ ፕሮቲን (spike glycoprotein) እንዲሰራ ያደርጋል። ሰውነታችን ይህን አዲስ የተመረተ ፕሮቲን የሚያጠፋ አንቲቦዲ (antibody) ማምረት ይጀምራል። ይህ አዲስ የተመረተ አንቲቦዲ ሰውነትን ከኮቪድ-19 ቫይረስ ይከላከላል።

የክትባቱ የጎን ጉዳት (Side effects)

ክትባቱን የሚወስዱ ሰዎች ላይ ሁሉም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ። እንደትኩሳት እና ቁርጥማት ያለ ቀላል ህመም ክትባቱ ለመስራቱ ምልክት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ከባድ ወይም ለየት ያለ ህመም ካጋጠመ ለህክምና ተቋም ያሳውቁ። ፋርማሲ ሄደው ምክር መጠየቅ ይችላሉ።

በሙከራ ጊዜ (Clinical Trial) የታዩ የህመም ምልክቶች

መርፌው የተወጋበት ቦታ የሚሰማ ህመም

Pain at the injection site

ድካም ወይም እስትራፓ

Fatigue

ራስምታት

Headache

የጡንቻ ህመም

Myalgia

ብርድ ብርድ ማለት

Chills

የመገጣጠሚያ ህመም

Joint pain

ትኩሳት

Fever

መርፌ የተወጋበት ቦታ ማበጥ

Injection site swelling

መርፌ የተወጋበት ቦታ መቅላት

Injection site redness

ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ

Nausea and vomiting

ንፍፊት አከባቢ ማበጥ እና ማመም

Axillary swelling/tenderness

 

የሞደርና ኮቪድ 19 ክትባት መውሰድ የሌለባቸው ሰዎች

  • ለዚህ ክትባት ወይም በውስጡ ለሚገኙ ኬሚካሎች አደገኛ አለርጂ (ለምሳሌ Anaphylaxis) ያለባቸው ሰዎች ይህንን ክትባት መውሰድ የለባቸውም።

በዚህ ክትባት ውስጥ የሚገኙ ኬምካሎች ዝርዝር

1. Messenger ribonucleic acid (mRNA)

2. Lipids

  • SM-102
  • Polyethylene glycol [PEG] 2000 dimyristoyl glycerol [DMG]
  • Cholesterol

3. 1,2-distearoyl-sn-glycero-3-phosphocholine [DSPC]

3. Tromethamine hydrochloride

4. Acetic acid

5. Sodium acetate

በክትባቱ የሙከራ ግዜ ጥቂት ሰዎች አናፍላክሲስ (Anaphylaxis) የሚባል አደገኛ አላርጂ አጋጥሟቸዋል።

አናፍላክሲስ የአለርጂ አይነት ነው። አንዳንድ ሰዎች ለብናኝ፣ ለምግብ አይነቶች፣ ወይም ኬሚካሎች እንዲህ ያለ አለርጂ ሊኖርባቸው ይችላል። አናፍላክሲስ ከሌሎቹ የአለርጂ አይነቶች የሚለየው ፈጣን ህክምና ካላደረጉ ለህይወት አስጊ በመሆኑ ነው።  የህመም ምልክቶቹ በደቂቃዎች ውስጥ ሊታዩ እና በፍጥነት ሊባባሱ ይችላሉ። ነገር ግን በግዜ ምልክቱን ካወቁ እና ተገቢውን ህክምና ካደረጉ በቀላሉ ይድናል።

የአናፍላክሲስ የህመም ምልክቶች ከንፈር እና ጉሮሮ አከባቢ የማበጥ እና የመብላት/የማሳከክ ስሜት፣ የጉሮሮ መዘጋት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የቆዳ መቅላት ማሳከክ እና ማበጥ፣ የልብ ትርታ መቀነስ፣ የማዞር ስሜት እና ራስን መሳት ሊሆኑ ይችላሉ። አነዚህ ምልክቶች ከታዩ ታማሚው ኢፕነፍሪን (Epi-pen/epinephrine) የተባለ መዳኒት ማግኘት አለበት። ወድያው የህክምና ባለሙያ እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው።

ይህን ክትባት የሚሰጡ ተቋሞች ሁሉ የአናፍላክሲስ መድሀኒት የሆነው ኢፕነፍሪን (epinephrine) እንዲኖራቸው በህግ ይገደዳሉ። ተከታቢዎች በክትባት መስጫው አከባቢ ሳይርቁ ለ15 ደቂቃ ያህል እንዲቆዩ ይመከራል። ይህም ተከታቢው የአናፍላክቲክ ህመም ምልክቶች ካሳየ አስፈላጊውን ህክምና ለማድረግ ይረዳል። ነገር ግን ተከታቢው ከክትባት ጣቢያው ከራቀ በኋላ ምልክቶች ካሳየ 911 በመደወል እርዳታ ማግኘት አለበት።

የኤፍድኤ(FDA) ማሳሰቢያዎች

  • የክትባቱን የጎን ጉዳት ለማስታገስ አድቪል (Advil/ibuprofen) ወይም ታይላኖል
  • ክትባቱን የሚወስዱ ሰዎች ላይ ያልጠበቀ አደገኛ አለርጂን በፍጥነት ለማከም ክትባቱ በሚሰጥበት ቦታ ሁሉ የአደገኛ አለርጂ መዳኒት እንዲኖር ኤፍዲኤ (FDA) ያስገድዳል። ክትባት የወሰዱ ሰዎች ላይ ድንገተኛ የመተንፈስ ችግር፣ የምላስ ወይም የጉሮሮ ማበጥ ካጋጠመ የአደገኛ አለርጂ ምልክት ሊሆን ስለሚችል አፋጣኝ ህክምና ማግኘት አለባቸው።
  • የበሽታ መቋቋም ችሎታቸው የደከመ ሰዎች ከሌሎች ሰዎች ሲወዳደር ክትባቱ ኮቪድ-19ን የመከላከል ችሎታው ሊቀንስ ይችላል።
  • እርጉዝ፣ የሚያጠቡ ሴቶች እና ከ18 አመት በታች በሆኑ ልጆች ላይ የሚያሳየውን ጥቅም እና ጉዳት ለማወቅ በቂ መረጃ የለም።
  • ይህ ክትባት በኤፍድኤ (FDA) የተፈቀደው ለአስቸኳይ ችግር ጊዜ ነው። በዚህ መሰረት የተሰጠ ፈቃድ ኢዩኤ(EUA) ይባላል።

ኢዩኤ (EUA or Emergency Use Authorization) ምንድነው?

የአሜሪካ የጤና ጉዳይ የበላይ ተጠሪ አካል የሆነው ኤች ኤች ኤስ (HHS) በአገሩ ውስጥ አደገኛ እና አጣዳፊ (ለምሳሌ እንደኮቪድ-19 ያለ) ወረርሽኝ መኖሩን ሲያውጅ  በጥናት ላይ የሚገኝ ክትባት (ወይም መድሀኒት)  ጥናቱ ከመጠናቀቁ በፊት ያለውን መረጃ  በመገምገም ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ሊወስን ይችላል። ይህ የችግር ግዜ ልዩ ፈቃድ ወይም ኢዩኤ (EUA) ይባላል።

በዚህ መንገድ የሚወጡ መድሀኒቶች እና ክትባቶች መደበኛው የኤፍድኤ(FDA) ፍቃድ ላይኖራቸው ይችላል። ነገር ግን ካሉት አማራጮች ተጨማሪ የጤና እክል ሳያደርሱ ወረርሽኙን መግታት እንደሚችሉ በሚካሄደው ጥናት ማሳየት ከቻሉ ለህዝብ ጥቅም እንዲውሉ ልዩ ፍቃድ ይሰጣቸዋል። ይህ ፍቃድ መደበኛው የኤፍዲኤ ፍቃድ አይደለም። በኤች ኤች ኤስ (HHS) የታወጀው የወረርሽኝ ጊዜ አዋጅ ሲነሳ ልዩ ፈቃዳቸው ያበቃል። ከዛ በሁዋላ አምራቾቹ ክትባቱን ለህዝብ ለማቅረብ ከፈለጉ መደበኛውን የኤፍዲኤ(FDA) ፍቃድ ማውጣት ይኖርባቸዋል።

ይህን ክትባት ከወሰዱ በሁዋላ ሰዎች ከፍተኛ የጤና እክል ቢደርስባቸው ምን ማድረግ ይችላሉ?

ቪ ሴፍ (V-safe)

ክትባት የወሰዱ ሰዎች ስለ ቪ ሴፍ (V-safe) የሚያብራራ ካርድ ይሰጣቸዋል። ቪ ሴፍ(V-safe) ለዚህ ክትባት ተብሎ የተዘጋጀ የስልክ እፕ(App) ነው። በቴክስት ሜሴጅ እና ሌሎች የስልክ አገልግሎቶች በመጠቀም የተከተበውን ሰው ጤንነት ለመከታተል ይረዳል። በ ቪ ሴፍ በኩል እንደአስፈላጊነቱ ከባለሙያ ጋር መማከር፣ በክትባቱ ምክንያት የተከሰተ የጤንነት ችግርን ለማሳወቅ፣ እንዲሁም የሁለተኛው የክትባት ግዜ ሲደርስ ተከታቢውን ለማስታወስ ይረዳል። በቪ ሴፍ መሳተፍ እና አለመሳተፍ የተከታቢው ምርጫ ነው።

በተጨማሪ ይህን ክትባት ወስደው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች የደረሰባቸውን ጉዳት ለኤፍዲኤ(FDA) በሚከተለው ዌብሳይት  ማቅረብ ይችላሉ

ለክትባቱ አምራች እና አቅራቢ የደረሰባቸውን ጉዳት ለማስታወቅ የሚከተሉትን መንገዶች መጠቀም ይቻላል

  • ዌብሳይት ModernaPV@modernatx.com
  • ስልክ ቁጥር 1-866-MODERNA (1-866-663-3762)
  • ፋክስ 1-866-599-1342

በአሜሪካ ነዋሪ ለሆኑ ሰዎች በዚህ ክትባት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን የሚረዳ አካል አለ። ስለዚህ የበለጠ መረጃ ማግኘት የሚፈልጉ ሰዎች ይህንን ድረገጽ ኢሜይል ወይም ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ

የሞደርና ኮቪድ 19 ክትባት ጥቅም/ጉዳት ለመመዘን የተደረገ ጥናት (Clinical Trial)ዋና ዋና ነጥቦች

ይህ ጥናት ራንደማይዝድ፣ ፕላሲቦ ኮንትሮል ያለው እና ብላይንድ (randomized, controlled, observer blind trial) ነው። ጥናቱ የተካሄደው በሰሜን አሜሪካ (USA) ነው።

ይህ ጥናት ያካተታቸው ሰዎች

እድሜያቸው 18 አመት በላይ ነው።

ለዚህ ጥናት ተመልምለው ቢያንስ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ያገኙ ሰዎች ብዛት

  • አጠቃላይ 30,351
  • ክትባቱን ያገኙ 15,185
  • ፕላሲቦ የተሰጣቸው 15,166

በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት ሰዎች በዘር እና በጾታ

  • ሴቶች 47.3%
  • ነጭ አሜሪካኖች 79.2%
  • ጥቁር አሜሪካኖች 10.2%
  • ሂስፓኒክ ወይም ላቲኖ 20.5%
  • ኤስያን6%
  • አሜሪካን ኢንድያኖች እና የአላስካ ኔቲቭ 0.8%
  • ሰሜን ሀዋሂ እና ፓስፊክ አይላንድ 0.2%
  • ከተለያየ ዘር የተወለዱ 2.1%
  • ሌሎች ያልተጠቀሰ 2.1% ናቸው።
  • ከጥናቱ በፊት ኮቪድ 19 የያዛቸው ሰዎች በዚህ ጥናት ውስጥ አልተጠቃለሉም።
  • የበሽታ መቋቋም ችሎታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ሰዎች (ለምሳሌ ኤድስ፣ የካንሰር ታማሚዎች፣ እና ሌሎች) በጥናቱ ውስጥ አልተጠቃለሉም። ግን ጤንነት ላይ የሚገኙ ኤች አይ ቪ ያለባቸው ሰዎች በጥናቱ ውስጥ ተጠቃለዋል።
  • ይህ ጥናት ገና አልተጠናቀቀም።
  • በጥናቱ የተጠቃለሉ ሰዎች ክትባት ከተሰጣቸው በሁዋላ በአማካኝ ለ28 ቀን ክትትል ተደርጎላቸዋል። 
  • በተጨማሪ የጤና ችግሮችን በተመለከተ መረጃ ለመሰብሰብ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ለሁለት አመት የሚቀጥል ክትትል እንደሚደረግላቸው ጥናቱ ላይ ተጠቅሷል።

የጥናቱ ውጤት ማጠቃለያ

(ይህ የክትባቱን በጤና ላይ የሚያስከትለውን ተፅህኖ ለማጥናት ከተወሰደው የሰዎች ብዛት ይለያል። ይህንን በጥልቀት ለማየት ከፈለጉ ወደኤፍዲኤ ወይም ፋይዘር ዌብሳይት ይመልከቱ።)

ኮቪድ-19ን የመከላከል ብቃቱ(Efficancy) በፐርሰንት

እድሜ

የመከላከል ብቃት

18 – 65 በታች

95.6%

65 እና በላይ

86.4%

ከክትባት በኋላ ኮቪድ 19 የያዛቸው ፕላሲቦ ከወሰዱ ሰዎች ጋር ሲነጻጸር

ክትባት የወሰዱ

እድሜ

ተሳታፊዎች ቁጥር

ኮቪድ 19 የያዛቸው*

18 – 65 በታች

10,551

7

65 እና በላይ

3,583

4

ፕላሲቦ የወሰዱ

እድሜ

ተሳታፊዎች ቁጥር

ኮቪድ 19 የያዛቸው*

18 – 65 በታች

10,521

156

65 እና በላይ

3,552

29

ክትባቱ በጤና ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ (Safety)

ክትባቱ በጤና ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ ላይ የተደረገው ውጤት በኤፍዲኤ(FDA) ድረገጽ ላይ በሰፊው ተዘርዝሯል። ለአጠቃላይ መረጃ ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ።

 ክትባት የተሰጣቸው (ቁ 15,185)ፕላሲቦ የተሰጣቸው (ቁ 15,166)
በአጠቃላይ የህመም ምልክት የታየባቸው ሰዎች23.9% (ቁ 3,632)21.6% (ቁ 3,277)
ሀይለኛ የህመም* ምልክት የታየባቸው ሰዎች1% (ቁ 147)1% (ቁ 153)

*ሀይለኛ የህመም ምልክት የሚወሰነው ተመራማሪዎቹ ቀድመው ባስቀመጡት መስፈርት ነው። ስእነዚህ መስፈርቶች የበለጠ ለማወቅ ወደኤፍዲኤ(FDA) ዌብሳይት ይመልከቱ።

ይህ እስከ ህዳር 25 2020 ድረስ በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ነው። ተሳታፊዎቹ ክትባት ከወሰዱበት ቀን አንስቶ ለ28 ቀን ክትትል ተደርጎላቸዋል።

ሌሎች ማጠቃለያዎች

  • በብዛት የሚታዩት ህመሞች መርፌ የተወጋበት ቦታ ህመም እብጠት እና መቅላት ነው።
  • ከመጀመሪያው ይልቅ ሁለተኛው ክትባት ሊያም ይችላል።
  • ከአደገኛ የህመም ምልክቶች መካከል ቤልስ ፓለሲ(3 ሰዎች)፣ የማያቋርጥ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ (1 ሰው) ይገኙበታል።

ማጣቀሻ

  1. Fact Sheet For Recipients And Caregivers Emergency Use Authorization (Eua) Of The Moderna Covid-19 Vaccine To Prevent Coronavirus Disease 2019 (Covid-19) In Individuals 18 Years Of Age And Older, https://www.cdc.gov/vaccines/covid-19/info-by-product/moderna/index.html, Accessed 12/2020
  2. Information about the Moderna COVID-19 Vaccine, https://www.cdc.gov/coronavirus/2019-ncov/vaccines/different-vaccines/Moderna.html, Accessed Jan 11, 2021
ቀን፦ 01/18/2021
  1.