Amharic Health Information

ቫይታሚን ቢ-1

ቫይታሚን ቢ-1  ብዙ ግዜ ታያሚን (Thiamin ወይም thiamine) ተብሎ የሚጠራ የቫይታሚን ቢ አይነት ነው። ሰውነት ጉልበት እንዲያገኝ፤ የተሟላ እድገት እና ጤንነት እንዲኖር ቫይታሚን ቢ-1   ያስፈልጋል

በቅርብ ግዜ እየተደረጉ ያሉ ጥናቶች የቫይታሚን ቢ-1 ለስኳር በሽታ፣ ከስኳር በሽታ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የነርቭ ህመም፣ ለልብ ድካም (heart failure)፣ እና ለአልዛሜር (Alzheimer’s) በሽታ  ያለውን ጥቅም እየመረመሩ ይገኛሉ። ይህን ቫይታሚን በመውሰድ እነዚህን በሽታዎች ማከም ወይም ምልክቶችን ለመቀነስ ይቻል እንደሆነ ወደፊት ከሚወጡት የጥናት ውጤቶች ግልጽ ይሆናል።

ከፍተኛ የቫይታሚን ቢ-1 መጠን የሚይዙ ምግቦች

ይህ ቫይታሚን ብዙ ምግቦች ውስጥ ይገኛል። ከእነዚህም መካከል

  • ስንዴ ገብስ እና የመሳሰሉ ጥራጥሬዎች
  • ስጋ እና አሳ
  • ለውዝ ባቄላ ሶያ አተር እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

የተሟላ ዝርዝር በዚህ ድረገጽ ያገኛሉ https://ods.od.nih.gov/pubs/usdandb/thiamin-content.pdf

ቫይታሚን ቢ-1 በመድሃኒት መልክ ይሸጣል?

ሁሌም ቫይታሚኖችን በክኒን መልክ ከመዋጥ ይልቅ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ማግኘት ይመረጣል። ሆኖም በክኒን መልክ መውሰድ ካስፈለገ ቫይታሚን ቢ-1 በክኒን መልክ ተዘጋጅቶ ይሸጣል።  ከቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የቫይታሚን ክኒኖች ወይም ከመልቲ ቫይታሚን ክኒኖች እንዲሁም ብቻውን ይሸጣል። ከፋርማሲ ሊገዙ የሚችሉ የቫይታሚን ቢ-1  ክኒኖች በተለያየ ስም እና አይነት ሊመጡ ይችላሉ። ለምሳሌ ታያሚን ሞኖናይትሬት (thiamin mononitrate) ታያሚን ሀይድሮ ክሎራይድ (thiamin hydrochloride) እንዲሁም ቤንፎታያማይን (benfotiamine) የተለመዱት ናቸው። 

በቀን ለሰው የሚያስፈልገው የቫይታሚን ቢ-1  መጠን እንደ እድሜ ክልል እና ጾታ የተለያየ ነው። የሚከተለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ

የእድሜ ክልል/ፆታ

በቀን የሚያስፈልገው መጠን በሚሊግራም (mg)

እስከ 6 ወር እድሜ ያሉ ህጻናት

0.2

ክ 6 – 12  ወር ያሉ ህጻናት

0.3

ከ 1 – 3 አመት እድሜ

0.5

ከ 4 – 8 አመት እድሜ

0.6

ከ 9 – 13 አመት እድሜ

0.9

ከ 14 – 18 ወንድ ልጆች

1.2

ከ 14 – 18 ሴት ልጆች

1.0

ወንድ ከ19 አመት በላይ

1.2

ሴት ከ19 አመት በላይ

1.1

እርጉዝ ወይም የምታጠባ ሴት

1.4

በሰውነት የቫይታሚን ቢ-1 እጥረት ሲኖር ምን ምልክት ይታያል?

የተመጣጠነ ምግብ በመብላት በቀን የሚያስፈልገውን የቫይታሚን ቢ-1 መጠን ማግኘት ይቻላል። ሆኖም አልፎ አልፎ የቫይታሚን ቢ-1  እጥረት ሊያጋጥም ያጋጥማል። የሚከተሉት ሁኔታዎች ለቫይታሚን ቢ-1 እጥረት ሊያጋልጡ ይችላሉ፦

  • የአልኮል መጠጥ ማዘውተር
  • የእድሜ መግፋት (ከስልሳአምስት አመት እድሜ በላይ)
  • የስኳር በሽታ
  • ኤች-አይ-ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS)
  • የሚከተሉትን መድሀኒቶች የሚወስዱ ሰዎች
    • ፊውሮስአማይድ (Furosemide)/ላሲክስ (Lasix)) (በውሀ መጠራቀም ምክንያት የሚፈጠር የሰውነት እብጠትን የልብ በሽታን እና አንዳንዴ የደም ግፊትን ለማከም የሚታዘዝ መድሀኒት)
    • ፍሎሮዩራሲል (Fluorouracil)/ አድሩሲል(Adruci) (አንዳንድ የካንሰር አይነቶችን ለማከም የሚታዘዝ መድሀኒት)

ከላይ የተጠቀሱት በሽታዎች ያለባቸው ህመምተኞች  ቫይታሚን ቢ መውሰድ ይጠቅማቸው እንደሆነ  ከሀኪማቸው ጋር መማከር ጥሩ ነው።

ከፍተኛ የቫይታሚን ቢ-1 እጥረት ሲኖር በሪበሪ (Beriberi) የሚባል በሽታ ሊያመጣ ይችላል። የዚህ በሽታ የህመም ምልክቶች የትንፋሽ ማጠር  ለመናገር መቸገር የእግር መደንዘዝ ናቸው። እንዲሁም  የአይን ህመም (ያለህመምተኛው ፍላጎት በራሱ መንቀሳቀስ) የእግር ማበጥ  ፓላይዝድ መሆን ሊከሰት ይችላል። እነዚህ የህመም ምልክቶች ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ።  በሪበሪ በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች ውስጥ የሚታይ ህመም ነው።

ሌላ ከፍተኛ የሆነ የቫይታሚን ቢ-1  እጥረት ዋርኒክ ኮርሳኮፍ (Wernicke-Korsakoff syndrome) የተባለ ህመም ሊያስከትል ይችላል። በዚህ ብዙ ግዜ የሚጠቁ ሰዎች ለረጅም ግዜ የአልኮል መጠጥ ሱስ (alcohol use disorder) ያለባቸው ሰዎች  ናቸው። የህመም ምልክቶቹም ከላይ የተጠቀሱት የበሪበሪ ምልክቶችን ጨምሮ የእጅ እና የእግር መደንዘዝ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ ያሉበትን ቦታና ግዜ መለየት መቸገር እና ያልተለመደ አይነት ግራ መጋባት ናቸው። እነዚህ የህመም ምልክቶች ከሰው

ይህ ቫይታሚን ከሚመከረው መጠን በላይ ቢወሰድ ለሰውነት ጉዳት አለው?

በከፍተኛ የቫይታሚን ቢ-1 በመውሰድ  ምክንያት የሚመጣ የጤና ጉዳት እጅግ ያልተለመደ ነው። ብዙ ምንጮች የማያስፈልግ የቫይታሚን ቢ-1 መጠን ሰውነታችን ውስጥ ከመጠራቀሙ በፊት ወደሰውነት መስረጉ ስለሚቀንስ (decrease absorption) እና በሽንት መልክ ከሰውነት ስለሚወጣ ነው ብለው ይጠቁማሉ። 

የበለጠ መረጃ ስለቫይታሚን ቢ-1 ለማግኘት ይህን ድረገጽ የመልከቱ

https://ods.od.nih.gov/factsheets/Thiamin-HealthProfessional/

 

ቀን:  Sep, 29, 2020